በዛሬው ዕለት ተጨማሪ 88 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

72

አዲስ አበባ ግንቦት 16/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 4048 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 88 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በዚህም በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 582 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከ 8 እስከ 75 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ 51 ወንድና 37 ሴት ሲሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 73 ሰዎች ከአዲስ አበባ( 19 ሰዎች በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ 1 ሰው የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለው፣ 53 ሰዎች ደግሞ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው) መሆናቸውም ተገልጿል።

ስምንት ሰዎች ከትግራይ ክልል( ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው)፣ 4 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል( 2 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸውና 2 ሰዎች ደግሞ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከታያዙ ሰዎች ጋር ግንኙነት የሌላቸው) ሲሆን ነዋሪነታቸውም አምቦ፣ ቡራዩ፣ ሰንዳፋና ሞጆ ከተሞች ናቸው።

አንድ ሰው ከሀረሪ ክልል( በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት) እንዲሁም 2 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ናቸው።

ተጨማሪ አንድ ሰው ከበሽታው ያገገመ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 152 ናቸው።

እስካሁን 81,010 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

የቫይረሱ ስርጭት ከቀን ቀን እየጨመረ በመሆኑ ህብረተሰቡ የጥንቃቄ መመሪያዎችን በትክክል መጠበቅ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም