ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሐምዶክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ   ግንቦት  13/2012 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ እና ከፍተኛ የልዑካን ቡድናቸው፣  ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሐምዶክ ጋር በኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪይ ተወያዩ።

በቪድዮ ኮንፍረንስ ባደረጉት ውይይት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያልተቋጩ ጉዳዮችን ለማጠናቀቅ እና የተዛቡ ግንዛቤ ዎችን  ማጥራትን ያለመ ነው ተብሏል።

በዋናነትም የአካባቢ ጥበቃ፣ የግድቡ የደኅንነት ሁኔታ እና የመረጃ ልውውጥን ስለ ማመቻቸት፣ በሱዳን በኩል ለተነሱት ጉዳዮች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የግድቡን  ወቅታዊ የሥራ ክንውንም ገልጸዋል።

አክለውም፣ የሕዳሴው ግድብ ለተፋሰሱ ሀገራት ኢኮኖሚ መጠናከር ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

የቴክኒክ ውይይቱን በሁለቱ ሀገራት የውኃ ሚኒስትሮች አማካኝነት ለመቀጠል ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ምንጭ፡ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም