ቀጥታ፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን የመቆጣጠሪያ መንገድ የተጠናከረ የመከላከል ስራ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13/2012 ዓ.ም ( ኢዜአ) የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን የመቆጣጠሪያ መንገድ የተጠናከረ የመከላከል ስራ መሆኑን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የውጭ አገር የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱ ወረርሽኙ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን እንደሚያሳይ ተገልጿል።

የህገመንግስት ትርጉም ጥያቄ ላይ ያተኮረ የባለሙያዎች ማብራሪያ እየተካሄደ ነው።

እየተካሄደ ባለው መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ እንደገለጹት፤ በበሽታው በተለይ በአዲስ አበባ ሁለት ክፍለ ከተሞች አሳሳቢ ሆኗል።

''ምንም አይነት የታወቀ ከቫይረሱ ከተያዘው ሰው ጋር ግንኙነትና ንክኪና የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ ነው'' ብለዋል።

ይህም ቫይረሱ ስርጭቱን በማህበረሰብ ውስጥ  መጀመሩን ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ 50 በመቶ ሲሆን ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ በከተማዋ ሁሉም ክፍለ ከተማ በሚባልበት ደረጃ ሪፖርት ያደረጉበት እና በተለይ በሁለት ክፍለ ከተሞች በልደታ እና አዲስ ከተማ በጣም ስር እየሰደደ መሆኑን ገልጸዋል።

በአንድ ግለስብ አማካኝነት በርካታ ሰዎች እየተያዙ እንደሆነ ጠቁመው፤ ''በሽታው በማህበረሰብ ውስጥ እየተስፋፋ በመሆኑ ከፍተኛ ርብርብ ያስፈልጋል'' ብለዋል።

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ 15 በመቶ የሚሆኑት ምንም የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ሰዎች ሆነው መገኘታቸውን ዶክተር ኤባ ጠቁመዋል።

አሁን እየተሰራ ካለው ስራ ተጨማሪ የተጠናከረ ስራ ካልተሰራ ወረርሽኙ በሌሎች አገሮች እያስከተለ ያለው አስከፊ ጉዳት ሊከሰት እንደሚችል ገልጸዋል።

የተለያዩ ስራዎች በተቀናጀ መልኩ እየተሰሩ ቢሆንም በአገር ደረጃ ያለው የወረርሽኙ ተጋላጭነታችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንም ተናግረዋል።

እየጨመረ የመጣው አገራዊ የመመርመር አቅም ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝም ተናግረዋል።

ቫይረሱን የመመርመር አቅም ምንም ካልነበረበት በክልል 16 እና በፌዴራል 8  ምርመራ የሚያደርጉ ላቦራቶሪዎች መደራጀታቸውን ጠቁመው፤ ሁሉም አገራት በተመሳሳይ ችግር ላይ ያሉ በመሆኑ የግብዓት እጥረት መኖሩን ጠቁመዋል።

''የአገራችን የመመርመር አቅም ውስንነት ቢኖርም ቫይረሱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፣ ተጋላጭነታችንም እየጨመረ መጥቷል'' ብለዋል።

''በመሆኑም በአገራችን ብቸኛው ወረርሽኙን የመቆጣጠር መፍትሄ መከላከል ነው'' ብለዋል።

መከላከል ሲባል ሰዎች የሚበዙበት ቦታ ያለመሄድ፣ እጅን መታጠብ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ የማድረግ ተግባራትን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም