ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ በሀሰተኛ ዘገባዎች አዝኛለሁ አለ

አዲስ አበባ ግንቦት 13/2012 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ  ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን በቀረበው ሀሰተኛ ዘገባ ማዘኑን ገለፀ።

ተቋሙ   የሚሰበስበውን ገንዘብ አለአግባብ ጥቅም ላይ አውሏል  በሚል በአንዳድ የመገናኛ ብዙሃን የቀረበው የተሳሳተ ዘገባ  እንዳሳዘነው  ለኢዜአ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

 ትረስት ፈንዱ የፋይናንስ አሠራር እና ደንብ  ያልተከተለ ምንም አይነት የገንዘብ  አጠቃቀም አሁንም ሆነ ለወደፊቱ እንደማይኖር አረጋግጧል፡፡

ተቋሙ ከ25 ሺህ በላይ ለጋሾች  6.36 ሚሊዮን ዶላር ከሰበሰበው 1.173 ሚሊዮን ዶላር   ለወረርሺኙ  መከላከል የሚውሉ  የህክምና ዕቃዎች ገዝቶ ወደ ሀገር ቤት  መላኩን ጠቁሟል፡፡

በዚህም መሰረት ተቋሙ የሚሰበስበውን ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ ብቻ በማዋል  ብክነትንና ስርቆትን ለመከላከል የሚያስችል  ስርአት መዘርጋቱን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም