ከባንኮች በጥሬ ገንዘብ ወጪ የሚደረግ የብር መጠን ላይ ገደብ ተጣለ - ኢዜአ አማርኛ
ከባንኮች በጥሬ ገንዘብ ወጪ የሚደረግ የብር መጠን ላይ ገደብ ተጣለ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11/2012 ዓ.ም ( ኢዜአ) ከባንኮች በጥሬ ገንዘብ ወጪ የሚደረግ የብር መጠን ላይ ገደብ መጣሉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ።
በግለሰብ ደረጃ በቀን እስከ 200 ሺህ ብር በወር ደግሞ እስከ 1ሚሊዮን ብር፣ በኩባንያ ደረጃ በቀን እስከ 300 ሺህ ብር በወር እስከ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ብቻ ማውጣት እንደሚቻል ነው ባንኩ ያስታወቀው።
ባንኩ ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀ መመሪያ ያወጣ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ነው የተባለው።
ከዚህ ውጭ ክፍያዎችን መፈጸም የሚችሉት ከአካውንት ወደ አካውንት፣ በቼክና በሲፒኦ እንዲሁም በሌሎች በኤሌክትሮኒክስ አማራጮች ብቻ ነው።
የብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ እንደገለጹት፤ ''ይህ መመሪያ በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ላይም ተግባራዊ ይደረጋል'' ብለዋል።
የመመሪያው አስፈላጊነትም ወንጀሎችን ለመከላከል፣ የግብር ስወራን ለመከላከልና ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመቀነስ ነው ተብሏል።