ቀጥታ፡

በሀዲያ ለኮሮና ቫይረስ መከላከል የሚውል 17 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተሰበሰበ

ሆሳዕና፣ ግንቦት 11/2012 ዓ.ም (ኢዜአ) በሀድያ ዞን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የሚውል 17 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የዞኑ አስተዳደር ገለፀ ።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪና የኮሮና መከላከል ግብረ ሀይል ሰብሳቢ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ ለኢዜአ እንዳሉት በዞኑ ቫይረሱን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ግብረ ኃይል በማቋቋም የማስተማርና ሌሎች ተግባራት ሲከናወን ቆይቷል።

ችግሩ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የተለያየ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ መከናወኑን ገልፀዋል ።

በዞኑ በሽታው ቢከሰት የለይቶ ማከሚያና ማቆያ ማዕከላት እንደተዘጋጁና አስፈላጊ የህክምና ቁሳቁስ እንደተሟላላቸው ጠቁመዋል።

ለቫይረሱ ተጋላጭ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ማገዝ የሚያስችል በአይነትና በጥሬ ገንዘብ 17 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ህብረተሰቡ የመዘናጋት ሁኔታ እየተስተዋለበት መሆኑን የጠቆሙት ዋና አስተዳዳሪው አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሱን ከቫይረሱ እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

በሆሳዕና ከተማ ቦብቾ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ደምሳሽ ተመስገን እንዳሉት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር በሚደረገው ርብርብ ውስጥ ባለሀብቱና ግለሰቦችም ጭምር ከመንግስት ጎን በመቆም አጋርነታቸውን ማረጋገጥ ይገባቸዋል።

ወረርሽኑን ለመከላከል ይረዳ ዘንድ አንድ መቶ ሺ ብር ግምት ያለው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ እንዳደረጉና ቀጣይም የሚጠበቅባቸውን ሁሉ በማድረግ ለችግሩ የመፍትሄ አካል ለመሆን መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

በሀገሪቱ የኮሮና ወረርሽኝን መከላከልና መቆጣጠር ለውሱን አካላት ብቻ የሚሰጥ ተግባር ሳይሆን ሁሉም ህብረተሰብ ተቀናጅቶና ተረዳድቶ መፍትሄ ማምጣት እንዳለበት የተናገሩት አቶ አየለ ኤርቃሎ ናቸው።

"እኛ ኢትዮጵያውያን የመረዳዳትና የመተጋገዝ ባህላችንን በማጎልበት ይህንን አስቸጋሪ ወቅት ማለፍ ግዴታችን ነው" ብለዋል።

ለችግሩ የመፍትሄ አካል ለመሆን የአንድ መቶ ሺ ብር ድጋፍ ማ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም