ቀጥታ፡

የቻይናው የምድር ባቡር ኩባንያ ኮሮናን ለመከላከል 910 ሺህ ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ግንቦት 8/2012 ዓ.ም (ኢዜአ) - የቻይናው ሲ.አር.ኢ.ሲ የምድር ባቡር ኩባንያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል 910 ሺህ ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ኩባንያው ለኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን 36 ሺህ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎች፣ 10 የሙቀት መለኪያዎችና 200 ሺህ የእጅ ጓንቶችን ነው።

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል ከኮርፖሬሽኑ ተወካይ ሊ ዜንግዌይ ተረክበዋል።

ዶክተር ስንታየሁ ድጋፉ የኮሮና ወረርሽኝ የሚያመጣውን የጤና ጉዳት ለመከላከል ይረዳል ብለዋል።

ወረርሽኙን ለመከላከል ዓለም አቀፍ ትብብር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ትብብሩ ወረርሽኙ የሚያመጣውን ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ለመቀነስም እገዛ እንዳለው አስታውቀዋል።

ድጋፉ አገሮቹ ያላቸውን ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚያደርሰው እምነታቸውን ገልጸዋል።

ተወካዩ በበኩላቸው ዓለም የገጠማትን አስቸጋሪ ወቅት በጋራ ተዋግቶ ማሳለፍ እንደሚገባ ገልጸው፤ ''ከተባበርን ቫይረሱን ማሸነፍ እንችላለን'' ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም