ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር የተመራውን ልዑካን ቡድን አነጋገሩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር የተመራውን ልዑካን ቡድን አነጋገሩ
አዲስ አበባ ግንቦት 8/2012 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ በሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር በአምባሳደር ዑመር ባሕር ማኔስ የተመራውን ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ከሚኒስትሩ ጋር ያደረጉት ውይይት በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ በድንበር ማካለልና በኢኮኖሚ ትሥሥር ላይ ያተኮረ ነበር።
እንዲሁም ዓለም አቀፍ ስጋት የሆነው የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ተጽዕኖ በጋራ መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል።
በሚኒስትሩ የተመራ ቡድን ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ሲገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው ተቀብለውታል።
ኢትዮጵያ ሱዳን የረጅም ጊዜ ታሪካዊና ባህላዊ ወዳጅነትያላቸው ሲሆን፣ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን በይፋ የጀመሩት እኤአ 1959 መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።