ቀጥታ፡

በጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ የተመራ ልዑካን ቡድን የጎንደር ዩኒቨርስቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎበኘ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2012 (ኢዜአ) በጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የተመራ ልዑካን ቡድን በጎንደር ዩንቨርስቲን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚገኘውን የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ህክምና ማዕከልን ጎበኘ።

በጉብኝቱም ከጤና ሚኒስትሯ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተና የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ተገኝተዋል።

ማዕከሉ ለኮሮናቫይረስ ህክምና የሚውል 320 አልጋዎችን ያዘጋጀ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 24ቱ ለጽኑ ህሙማን የሚውሉ ናቸው።

ልዑኩም  በተመሳሳይ በከተማው የተዘጋጁ የለይቶ ማቆያዎችንም ይጎበኛል።

በተጨማሪም በባህር ዳር ከተማ መሰል ጉብኝቶችን እንደሚያካሂድ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም