ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ሳያደርጉ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ300 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2012 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ሳያደርጉ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ300 በላይ ሰዎችን ፖሊስ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር አውሏል።

የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመከላከል በተለይም ሰው በሚበዛባቸው አካባቢዎችና የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ማድርግ ግደታ መደረጉ ይታወቃል።

ይሁን አንጂ በመዲናዋ በተለይም ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ርቀታቸውን ሳይጠብቁና ያለ ማስክ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች እየተበራከቱ መጥተዋል።

በመሆኑም ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ፤ በጦር ሃይሎች፣ ሜክሲኮ እና ተክለሐይማኖች አካባቢዎች ባደረገው ቁጥጥር ማስክ ሳያደርጉ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ300 በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

በትናንትናው እለት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከ1 ሺህ 300 በላይ ሰዎች ርቀታቸውን ሳይጠብቁና ያለ ማስክ ሲንቀሳቀሱ አግኝቷቸው በቁጥጥር ስር ማዋሉ ን መግለጹ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም