የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ 20 ሚሊዮን ዶላር ለሱዳን አበረከተች

64

አዲስ አበባ ሚያዝያ 27/2012 (ኢዜአ) የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ20 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ  ለሱዳን ድጋፍ አደረገች፡፡

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የልማት ፈንድ እንዳስታወቀው የሱዳንን መንግስት የጤና ሴክተር ለመደገፍ ግምታቸው 20 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን የህክምና ቁሳቁሶች   ለሱዳን

ረድቷል፡፡  

ከአረብ ኤሜሬትስ ለሱዳንን የተሰጠው የአሁኑ ድጋፍ ቀደም ሲል ኢምሬትስ ለሱዳን ለመስጠት ቃል ከተገባችው  የ1.5 ቢሊዮን ዶላር አካል መሆኑን ካኽሊጅ ታይምስ አስነብቧል፡፡

ድጋፉ በሱዳን የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ኤምባሲ እና በአገሪቱ ብሔራዊ የህክምና አቅርቦት ፈንድ በኩል በጋራ የሚከወን መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የመጀመሪያውና ሁለተኛው ዙር የ135 ቶን አቅርቦት እንደተላከና የቀረው ሶስተኛ ዙር ደግሞ በዚህ አመት መጨረሻ አንደሚላክ ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ቀደም አረብ ኤሜሬትስ የሱዳንን ኢኮኖሚ ለመደገፍ ለማዕከላዊ ባንኩ 250 ሚሊዮን ዶላር ስትለግስ ግምቱ 150 ሚሊዮን ዶላር የሆነ ለ400ሺ ተማሪዎች መግብነት የሚውል ስንዴ ደግሞ መርዳቷ ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም