የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት በመዲናዋ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት በመዲናዋ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26/2012 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት በአዲስ አበባ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።
የልማት ፕሮጀክቶቹ ጉብኝት እየተካሄደ ያለው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ መሪነት ነው።
ጉብኝቱ በምክትል ከንቲባው አስጎብኝነት በፒያሳ ጊዮርጊስ አካባቢ እየተገነባ ካለው የአድዋ ማእከል ግንባታ በማለዳ ተጀምሯል።
በመቀጠልም አራት ኪሎ አካባቢ እየተገነባ ያለውን ብሄራዊ ቤተ መፅሃፍት፣ በመስቀል አደባባይ እየተከናወነ ያለውን የልማት ፕሮጀክት የሚጎበኙ ይሆናል።