ቀጥታ፡

የሳንሱሲ ታጠቅ ኬላ የአስፋልት መንገድ ግንባታ መጓተቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2012( ኢዜአ) የሳንሱሲ ታጠቅ ኬላ የ13 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ በወሰን ማስከበር ችግር ምክንያት በተያዘለት ጊዜ ሊጠናቀቅ አለመቻሉ ተገለጸ።

የመንገዱ ግንባታ ከተጀመረ 2 ዓመት ከ5 ወራት የሆነውና አፈፃፃሙ 93 በመቶ መድረስ የነበረበት ቢሆንም አሁን ላይ 40 በመቶ ብቻ  መሆኑ ነው የተጠቀሰው።

የመንግዱን ግንባታ ሂደት በሚመለከት የኢትዮጵያ መንግዶች ባለስልጣን ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኝ፣ ሌሎች ከፍትኛ የስራ ሃላፊዎችና የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ጎብኝተዋል።

በስምምነቱ መሰረት የመንገዱ ግንባታ አሁን ላይ 93 በመቶ አፈፃፀም ላይ መገኘት የነበረበት ቢሆንም የወሰን ማስከበር ሳንካ ሆኖበት አፈፃፀሙ 40 በመቶ ብቻ መሆኑን ተመልክተዋል።

የሳንሱሲ ታጠቅ ኬላ የ13 ነጥብ 5 ሚሎ ሜትር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ በ820 ሚሊዮን ብር በመንግስት ወጭ በአንድ የግል ተቋራጭ ድርጅት እየተገነባ ያለ ፕሮጀክት ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም