የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 131 ሆኗል - ኢዜአ አማርኛ
የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 131 ሆኗል

ሚያዝያ 22/2012( ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1408 የላቦራቶሪ ምርመራ አንድ ሰው የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በዚህም በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 131 ደርሷል።
ቫይረሱ የተገኘባት የ45 ዓመት ኢትዮጵያዊት ስትሆን የባህርዳር ነዋሪና ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ንክኪ እንዳላት መረጋገጡም ተገልጿል።
አንድ ተጨማሪ ሰው ከበሽታው ያገገመ ሲሆን እስካሁን 59 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 67 ሰዎች በለይቶ ህክምና ውስጥ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ በቫይረሱ 3 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 2 የውጭ አገር ዜጎች ደግሞ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
በአሁኑ ወቅት በጽኑ ህክምና ክፍል ውስጥ የሚገኝ የኮሮናቫይረስ ታማሚ የሌለ መሆኑም ተገልጿል።