ቀጥታ፡

በትግራይ ኮሮናን ለመከላከል ከ600 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ተገኘ

መቀሌ ፣ ሚያዚያ 22/2012 (ኢዜአ) በትግራይ ክልል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያግዝ ከተለያዩ አካላት ትላንት በጥሬ ገንዘብ ከ600 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ተገኘ።

ድጋፉን ያደረጉት የመቀሌ መረዳጃ ማህበር ፣ በአሜሪካ የሚኖሩ የእንደርታ ልማት ማህበር አባላት፣ የትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የፖሊስ ስፖርት ክለብ ናቸው።

ከዚህም ውስጥ የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቫይረሱን  ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ ኃይል በገንዘብ ለማጠናከር ያሰባሰበው 326ሺህ 500 ብር ድጋፍ ይገኝበታል።

ሌላው በአሜሪካ የሚኖሩ የእንደርታ ልማት ማህበር ተወካይ መምህር ጠዓመ ግደይ እንዳሉት የኮሮና ቫይረስ በሽታ ለመከላከል ከህዝባቸው ጎን እንደሚቆሙ  ተናግረዋል።

ማህበሩ የላከው 170ሺህ ብር  ለክልሉ ሀብት ማሰባሰብ ንኡስ ኮሚቴ ግብረ ኃይል  አስረክበዋል።

ድጋፉን የተረከቡት በክልሉ የኮሮና መከላከል ግብረ ኃይል የሀብት  አሰባሳቢ ንኡስ ኮሚቴ አባል መምህር አሰፋ ገብረስላሴ  ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም