ቀጥታ፡

ኮሚሽኑ መደበኛ ባልሆነ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦችን ከመኖሪያቸው ማፈናቀል እንዲገታ አሳሰበ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 21/2012( ኢዜአ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መደበኛ ባልሆነ ቤት የሚኖሩ ቤተሰቦችን ከመኖሪያቸው በሃይል ማፈናቀል በጊዜያዊነት ሊታቀብ ይገባል ሲል አሳስቧል።

ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች የተከሰተውን መደበኛ ባልሆነ ቤት የሚኖሩ ቤተሰቦችን ማፈናቀል በጊዜያዊነት መቆም አለበት ብሏል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ "መደበኛ ያልሆነ የመሬት አያያዝ ና የቤት ግንባታ መስፋፋት አዲስ አበባን ጨምሮ በብዙ ከተሞች ትልቅ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ነው" ብለዋል፡፡

ሆኖም የኮሮና ቫይረስ በተከሰተበት በዚህ ወቅት ቤተሰቦችን በኃይል ከመኖሪያቸው ማስወጣት፣ ሴቶችና ሕጻናትን ጨምሮ "በተለይ ለመብት ጥሰት" ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ትልቅ አደጋ አለው በማለት ተናግረዋል፡፡

ይህ ቢሆንም በዚህ ወቅት የሚታዩ አዳዲስና መደበኛ ያልሆነ የመሬት አያያዝ ና መደበኛ ያልሆነ የቤት ግንባታን እንዲከላከሉ አሳስበዋል።

ነገር ግን በዚህ የአስቸኳይ ግዜ ዓዋጅ ወቅት መደበኛም ባይሆኑም፥ ነባር ነዋሪዎችን ከመኖሪያቸው በኃይል ማስወጣት ተገቢነት እንደሌለው ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም