በምርጫ ጉዳይ መንግስትና የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እየመከሩ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በምርጫ ጉዳይ መንግስትና የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እየመከሩ ነው
ሚያዝያ 21/ 2012 (ኢዜአ) "ኮቪድ19 ምርጫን ማራዘምና የህግ አማራጮች” በሚል ርዕስ መንግስት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
ኢትዮጵያ ለ6ኛ ጊዜ ልታካሂደው የነበረው የዘንድሮው ብሄራዊ ምርጫ ዓለም አቀፍ ስጋት ሆኖ ድንገት በተከሰተው የኮቪድ19 ወረርሽኝ ምክንያት በተያዘለት ጊዜ ማካሄድ እንደማይቻል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
በመሆኑም በዛሬው እለት "ኮቪድ19 ምርጫን ማራዘም እና የህግ አማራጮች” በሚል ርዕስ መንግስትና ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓረቲ አመራሮች እየመከሩ ነው።
በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ምክትል አቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ለውይይቱ መነሻ ሃሰብ አቅርበው ውይይቱ ቀጥሏል።
በውይይቱ መነሻ ሃሳብም ላይ አራት የተለያዩ የመፍትሄ አማራጮች ቀርበዋል።
ይሄውም፤
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን፤
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ፤
ህገ መንግስት ማሻሻል፤
የህገ መንግስት ትርጓሜ መጠየቅ የሚሉ ናቸው።
የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በእነዚህ ሃሳቦች ላይ በዝርዝር የሚያደርጉት ውይይትም እንደቀጠለ ነው።