ስለኮሮናቫይረስ ትክክለኛ መረጃ የሚሰጡ መልዕክት መላላኪያ ዘዴዎች በለጸጉ - ኢዜአ አማርኛ
ስለኮሮናቫይረስ ትክክለኛ መረጃ የሚሰጡ መልዕክት መላላኪያ ዘዴዎች በለጸጉ
አዲስ አበባ ሚያዚያ 20/2012(ኢዜአ) የጤና ሚኒስቴርና ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስለኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ትክክለኛ መረጃ የሚሰጡ የዋትስ አፕና ቴሌግራም መልዕክት መላላኪያ ዘዴዎችን አበለጸጉ፡፡
የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፤ ህብረተሰቡ ዘዴዎችን በመጠቀም ስለኮረናቫይረስ መረጃ ለማግኘት መጀመሪያ 0962228565 የሞባይል ቁጥር በስልክ ላይ መመዝገብ ያስፈልጋል።
ወይንም Gov't of Ethiopia Covid-19 በማለት የዋትስ አፕ ወይም የቴሌግራም ላይ በመፈለግ አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል።
ይህን ካደረጉ በኋላ ለዋትስ አፕ hi ብሎ በመላክ በምላሹ በአማርኛ የተዘጋጁ መልዕክቶች የሚላኩ ሲሆን የሚፈልጉትን መረጃ በመምረጥ መቀጠል ይችላሉ።
ለቴሌግራም ደግሞ start የሚለውን በመምረጥ በምላሹ በአማርኛ የተዘጋጁ መልክቶች የሚላክ ሲሆን ተጠቃሚዎች የሚፈልጉትን በመምረጥ መቀጠል እንደሚችሉ ተገልጿል።
እነዚህን አጠቃቀማቸው ቀላል የሆኑ የመልዕክት መላላኪያ አገልግሎት በኢትዮጵያ ከ3 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን የመድረስ አቅም አላቸው።
ኮቪድ-19ን የተመለከቱ መረጃዎችን ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንም በቀጥታ ትክከለኛውን መረጃ ለማግኘት ያስችላሉ።
እነዚህ የመረጃ መልዕክት መስጫ መተግበሪያዎች ስለኮቪድ-19 የህመም ምልክቶች፣ መደረግ ስላለባችው ጥንቃቄና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን ይሰጣሉ።
እንዲሁም የቫይሰሩን ስርጭትና አጠቃላይ ሁኔታ በአማርኛ ቋንቋ ለተጠቃሚዎች ያቀርባሉ።
በቀጣይ የተደራሽነት አድማስን ለማስፋት በሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መረጃዎችን እንደሚያቀርብም ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።