ቀጥታ፡

በህንድ በ20 ዓመታት ዝቅተኛውን የአየር ብክለት አስመዘገበች

ሚያዝያ 15/2012 (ኢዜአ) በህንድ ከ20 ዓመት ወዲህ ዝቅተኛው የአየር ብክለት መጠን መመዝገቡ ተገለጸ፡፡

በህንድ የምስራቁ  ክፍል  በተለይም ዋና ከተማዋ ኒው ዴልሂ   በበጋ ወቅት የአየር ሁኔታው እጅግ አስቸጋሪና በመሆኑ  ለመኖር ያዳግታል፡፡

 በአሁኑ ግዜ ኮሮና ባስከተለው የእንቅስቃሴ ገደብ በአገሪቱ ከሃያ አመታት ወዲህ እጅግ ዝቅተኛው የአየር  ብክለት እንዲመዘገብ ምክንያት መሆኑን  ሲኤንኤን ናሳን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

እንደ ናሳ ሪፖርት እ.ኤ.አ ከ2016 እስከ 2020 ባሉት ዓመታት ከመጋቢት መጨረሻ እስከ ሚያዚያ 5 ድረስ በወሰዳቸው  ስድስት የናሙና ቀናት ነው የአየር ብክለት መቀነሱን በጥናት የተረጋገጠው፡፡

ሪፖርቱ እንዳመለከተው በሚያዚያ ወር በአየር ላይ ከሚኖረው   በካይ ብናኝ መጠን አሁን ዝቅ ማለቱ ተጠቅሷል፡፡

ጥናቱ የተካሄደው በአመታቱ ውስጥ የተለቀቁ በካይ የብናኝ መጠኖችን በመመዝገብ ሲሆን፣ በኮሮና ምክንያት እንቅስቃሴ ሲገደብ የአየር ንብረት ለውጥ እንደሚከሰት አውቀን ነበር ሲሉም  የነሳ ተመራማሪው ፓዋን ጉብታ ተናግረዋል፡፡

በምዕራብ ህንድም የአየር ብክለት መጠኑ እንደቀነሰ የአገሪቱ የመሬት ምልከታ ጣቢያዎች ለናሳ መረጃ መስጠታቸው ተመልክቷል፡፡

ህንድ ባሰለፍነው መጋቢት ወር ለአምስት ሳመንታት የሚቆይ የእንቅስቃሴ ገደብ ማሳለፏ ይታወሳል፡፡

የአየር ንብረት ሁኔታን በሚመለከት በሚወጡ መረጃዎች መሰረት የበኮሮና ቫይረስ ባስከተለው የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ወደ ሰማይ የሚለቀቀው ጎጂ የብናኝ መጠን ቀንሷል፣ አለማችንም ንጹህ አየር እየተነፈሰች ትገኛለች፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም