በናይጄሪያ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ተከሰተ

58

ሚያዝያ 13/2012 ናይጄሪያ ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ  ከፍተኛ ነው የተባለውን የዋጋ ግሽበት አስተናግዳለች፡፡

የአገሪቱ ብሔራዊ የስታትስቲክስ ቢሮ እንዳስታወቀው ባለፉት 23 ወራት የናይጄሪያ የዋጋ ግሽበት በ12.6 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡

የሸማቾች የዋጋ መረጃ ጥናት እንዳረጋገጠው የዋጋ ግሽበቱ በየወሩ 0.6 በመቶ ጨምሯል፡፡

በሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት በሁሉም ምርቶች ላይ ቢስተዋልም በምግብ ምርቶች ላይ ብቻ ከየካቲት እሰከ መጋቢት ወር ከ14.90 በመቶ ወደ 14.98 በመቶ ከፍ ማለቱ ነው የተነገረው፡፡

በየጊዜው በሚለዋወጠው የግብርና ምረት ገበያ ላይ ግን የ0.3 በመቶ ለውጥ ብቻ እንዳሳየ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል ግሽበቱ ከከተማ ከተማ እንደሚለያይና በአንዱ ከተማ ሲጨምር በሌላኛው በመጠኑ የመቀነስ ሁኔታ እንደሚታይበት ሪፕልስ  ናይጄሪያ አስነብቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም