ኮቪድ-19 በኢኮኖሚው ላይ የሚያደርሰውን የከፋ ጫና ለመከላከል የተወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ...ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ

66

ሚያዝያ 13/2012 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ኮቪድ19 በኢኮኖሚው ላይ የሚያደርሰውን የከፋ ጫና ለመከላከል የተወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንሚቀጥል ተናገሩ፡፡

ከእርምጃዎቹ መካከልም የሠራተኞችን የሥራ ዋስትናን ማስጠበቅ፣ዘላቂ በሆነ መልኩ ገቢ እንዳይቋረጥ ማድረግ፣እጅግ ተጋላጭ የሆኑትን የማኅበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ የሚያደርጉ አሠራሮችን ማስፋፋት፣ የመሠረታዊ አቅርቦቶችን የግብይት ሥርዓት ማርጋት፤እንዲሁም ለአምራች ዘርፎች ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

ለምግብ ዋስትና የግብርናውን ዘርፍ አምራችነት ማረጋገጥ ወሳኝነት አለውም ብለዋል፡፡

ምንም ዓይነት የአቅርቦት እጥረት እንዳይከሠት የማዳበሪያ፣የምርጥ ዘር እንዲሁም የፀረ ተባይ መድኃኒቶች አቅርቦት ሳይቆራረጥ የሚቀጥልመሆኑንም ነው የገለፁት፡፡

የኢኮኖሚውን ዘርፍ መዳከም ሊያራዝሙ ከሚችሉ ሁኔታዎች አንዱ፣ተመጣጣኝ የሆነ የኅብረተሰብ ጤና ርምጃ አለመውሰድ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ፤ለኢኮኖሚው መረጋጋት ሲባል በሕክምናው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ሙዓለ ንዋይ በማፍሰስ ተመጣጣኝ የመከላከል ርምጃ መውሰድ እንደሚቀጥል ከፌስቡክ ገፃቸው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም