“ኢትዮጵያ ለኔ ቤቴ ነች”- ሶሪያዊው የሬስቶራንት ባለቤት - ኢዜአ አማርኛ
“ኢትዮጵያ ለኔ ቤቴ ነች”- ሶሪያዊው የሬስቶራንት ባለቤት
ሚያዝያ 13/2012 (ኢዜአ) አዲስ አበባ ውስጥ የመካከለኛው ምስራቅ ምግቦችን በማዘጋጀት ለደንበኞቹ የሚያቀርበው ሶሪያዊ ስደተኛ ኢትዮጵያ ሃገሩ እንደሆነች እንደሚሰማው ዘ ናሽናል ለተባለ የአረብ ኤሚሬትስ ድረገጽ ተናገረ።
በሶሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት ቤተሰቡን ከሙሉ ንብረቱ ጋር ያጣው አድና ሞሃመድ ሶሪያ ሁኔታዎች በመክፋታቸው ወደ ኢትዮጵያ ተሰዷል፡፡
ኑሮውን እንደ አዲስ በጀመረባት አዲስ አበባ ውስጥ የከፈታት አነስተኛ ምግብ ቤት ተቀባይነቱን እየጨመረችለት ራሱ የሚያዘጋጃቸውን ጣፋጭ ምግቦች ለደንበኞቹ እያቀረበ መሆኑን የሚናገረው አድና ስራው ከራሱ አልፎ ለሌሎችም ውሎ መግቢያ ሆናል ባይ ነው ።
በፈረንጆቹ 2015 የወተት ተዋጽኦ ምርቶች አለማቀፍ ኮንፈረንስ ተሳታፊ ለመሆን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ኑሮዬን ኢትዮጵያ ውስጥ እመሰርታለሁ ብሎ እንዳልጠበቀ የሚናገሩት ማትዝ ለባታር ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ምቹ የንግድ እንቅስቃሴ ወደዚህ ስራ እንዲገባ እንዳስቻለው ተናግሯል።
ማትዝ ላብሃር አዲስ አበባ ውስጥ አድና በከፈታት ሬስቶራንት ውስጥ በረዳት የምግብ ዝግጅት ባለሙያነት በመስራት በወር 950 የአሜሪካን ዶላር እያገኘ መሆኑን የሚያነሳው ዘገባው፤ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ከኤርትራ ፣ ከደቡብ ሱዳን ፣ ከሶማሊያ እና ከየመን የመጡ ስደተኞችን የምታስተናግድና ለሶሪያውያንም በሯን ያልዘጋች መሆናን አንስቷል።
ከኢትዮጵያዊት ሴት ጋር ትዳር መስርቶ በአሁኑ ወቅት የአንድ ልጅ አባት የሆነው የደማስቆ ተወላጁ አድና አማርኛ ቋንቋን አቀላጥፎ መናገር መቻሉ ቦሌ አካባቢ ለሚገኘው ምግብ ቤቱ ገበያውን ሞቅ እንዳደረገለት ተናግሯል።
ያሳለፋቸው ጊዜዎች በመጥፎ የእርስ በእርስ እልቂት ትዝታዎች የተሞሉ በመሆናቸው ወደ ሶሪያ የመመለስ ፍላጎት እንደሌለው የሚናገረው አድና ኢትዮጵያ ህይወትን ድጋሚ የጀመረባት ቤቱ እንደሆነች ለድረገጹ ተናግሯል።
በቀን 150 ምግቦችን አዘጋጅቶ ለደንበኞቹ ሲያቀርብና በጥሩ ሁኔታ እየሰራ እንደነበረ ያስታወሰው አድና በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት አብዛኞቹ ደንበኞቹ ቤታቸው ውስጥ በመሆናቸው ሽያጩ የቀዘቀዘ ቢሆንም ቫይረሱ ሲወገድ ወደ መደበኛ ህይወት እንደሚገባ ተስፋውን ገልጿል።
በርካታ ሶሪያውያን የአድና መሐመድን እና የማትዝ ሌብሃርን ፈለግ በመከተል ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ መሆኑን ያነሳው ድረገጹ ሶርያውያኑ በጎብኚዎች ቪዛ ወደ ኢትዮዽያ በመግባት በከተሞች ጎዳናዎች ላይ በልመና ስለመሰማራታቸው ተናግሯል።
አስፈላጊው ምዝገባ ቁጥጥርና ክትትል ያልተደረገባቸው ስደተኞች ሃገሪቱ ላይ ሊያስከትሉ ከሚችሉት ዘርፈብዙ ጫና አንጻር ኢትዮዽያ ጉዳዩ ላይ ከሚሰሩ ከአለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን የስደተኞችን ህይወት ሊያረጋጉ የሚችሉ በርካታ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡
ይህንን የሚነግሩንም በኢትዮዽያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ቃል አቀባዩ ክሱት ገብረእግዚያብሄር የጥገኝነት ማመልከቻ አስገብተው ድጋፍ እየተደረገላቸው ያሉት ጥቂት ስደተኞች ብቻ ናቸው ብለዋል።
ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ በግዛቷ ለሚኖሩ ስደተኞች ህጋዊ አሰራሮችን ተከትሎ መኖሪያ፣ የስራ እድልና ዜግነት የማግኘት መብቶችን ለመስጠት የሚያስችል ህግ ማወጣቷን የሚገልጸው ዘገባው የአውሮፓ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽንም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ የሚያግዝ ገንዘብ እንደለገሱ አስታውሷል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ዋቢ ያደረገው ድረገጹ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በዘለቀው ግጭት ከ5.6 ሚሊዮን በላይ ሶሪያውያን ከትውልድ አገራቸው መፈናቀላቸውን ጨምሮ ዘገቧል።