በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 108 ደረሰ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 108 ደረሰ
አዲስ አበባ ሚያዝያ 11/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 108 ደረሰ ፡፡
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው የ667 ላቦራቶሪ ምርመራ ሶስት ተጨማሪ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
በዚህም በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 108 ደርሷል።
ሶስቱም ሰዎች የኢትዮጵያ ዜጎች ናቸው፡፡
ከሶስቱ ሰዎች ሁለቱ ለይቶ መቆያ ውስጥ ያሉ ሲሆን፣ አንዲት የ52 ዓመት ኢትዮጵያዊት በበሽታው ከተያዘው ሰው ጋር የነበራት ግንኙነት እየተጣራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
እስከ አሁን በአገሪቱ በአጠቃላይ ለ7557 ሰዎች ምርመራ መደረጉ ተገልጿል፡፡
አሁን ላይ አንድ ታማሚ በጽኑ ህሙማን ህክምና መስጫ ውስጥ ሲሆን እስካሁን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 16 ደርሷል።