ቀጥታ፡

የፌዴራል የመንግስት መሰራተኞች የስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ተሻሻለ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 10/2012( ኢዜአ) በኮሮና ቫይረስ መከላከል ብሔራዊ ግብረ-ሃይል ውሳኔ መሰረት የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች የስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት መሻሻሉን የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ። 

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በዛብህ ገብረየስ ለኢዜአ እንዳሉት በኮሮና ቫይረስ መከላከል ብሔራዊ ግብረ-ሃይል ውሳኔ መሰረት የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች የስራ መግቢያ ሰዓት ጠዋት 1 ሰዓት ከ30 የስራ መውጫ ሰዓት ደግሞ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 እንዲሆን ተወስኗል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም