ቀጥታ፡

12 አባላት የያዘ የቻይና የሕክምና ቡድን አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 8/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያግዝ 12 አባላት ያሉት የቻይና የሕክምና ቡድን ኢትዮጵያ ገባ።

ቡድኑ የጸረ-ወረርሽኝ ህክምና ባለሙያዎች ያሉት ሲሆን ''በተባበረ ክንድ እናሸንፋለን'' በሚል መሪ ሃሳብ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ለኢትዮጵያ ድጋፍ ለማድረግ ከቻይና የመጣ ነው።

የሕክምና ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሬድዋን ሁሴንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም