ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ ሚያዚያ 2/2012 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ በቅርቡ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።

የምርመራ ላቦራቶሪው በጥቂት ቀናት ውስጥ ስራ የሚጀምር ሲሆን በቀን 50 ናሙናዎችን መርምሮ ውጤቱን የማሳወቅ አቅም አለው ተብሏል።

ይህም ኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል በምታደርገው ጥረት ተጨማሪ አቅም ሲሆን የመመርመር አቅምንም የሚያሳድግ ይሆናል።

ለዚሁ ምርምራ ያለውን ዝግጁነት በሚመለከት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ እና የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ጣሰው ወልደ ሃና ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም