በህንድ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ከ250 ሺህ ብር በላይ ለገሱ

66

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2012 (ኢዜአ) በህንድ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የሚማሩ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ከ250 ሺህ ብር በላይ ለገሱ።

በህንድ ኒውዴልሂ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለኢዜአ እንዳስታወቀው በህንድ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የሚገኙ ተማሪዎች በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ለሚከናወነው ተግባር ይረዳ ዘንድ ነው ገንዘቡን የለገሱት።

በህንድ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዶክተር ትዝታ ሙሉጌታ እንደገለጹት ኤምባሲው በኢሜይል፣ እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያና ምስል በተቀነባበረ ዘዴ ለተማሪዎቹ ስለ ወረርሽኙ አስከፊነትና ጥንቃቄ ሲያስገነዝብ ቆይቷል።

ከዚህ ባሻገር የገንዘብ ማሰባሰብ ማከናወኑንና ተማሪዎቹ ከ250 ሺህ ብር በላይ መለገሳቸውን ገልጸው ተማሪዎቹ ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም