የተለያዩ ድርጅቶች ለኮሮና መከላከያ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
የተለያዩ ድርጅቶች ለኮሮና መከላከያ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ መጋቢት 29/2012(ኢዜአ) የተለያዩ ድርጅቶች የኮሮናቫይረስ ስርጭትን መከላከያ የሚውል ከ16 ሚሊዮን በላይ ብር እና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ ።
ከደርጅቶቹ መካከል ዘመን ባንክ 5 ሚሊን ብር ለብሄራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ ሃይል ገቢ ያደረገ ሲሆን ለጤና ተቋማት ድጋፍ የሚውልም ተጨማሪ 800 ሺህ ብር ለጤና ሚኒስቴር አስረክቧል።
ረጲ የሳሙና ፋብሪካም 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት የንፅህና መጠበቂያ ቁሰሳቁስ አበርክቷል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር፣ ኒያላ ሞተርስ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር እና ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የ1ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት 650 ሺህ ብር፣ ፣ ኢትዮ ታካሞል የተባለው ድርጅትም 500 ሺህ ብር እና ኢትዮጵያ ባይብል ፎረም የ100 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ እና የኮሮና ቫይረስ ብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ምስጋናዉ አረጋ የተደረገዉ ድጋፍ አመስግነው መንግስት ለሚያደርገዉ ዝግጅት አጋዥ እንደሚሆን ገልፀዋል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሰሃርላ አብዱላሂ በበኩላቸው እንደዚህ አይነት ድጋፎች ተጠናክረዉ መቀጠላቸዉ አገራችን ለገጠማት ፈተና ጉልህ እገዛ አለው ብለዋል።
የኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር አበራ በቀለ እንዲህ ዓይነት ድጋፍ ለሰዉ ልጆች አስፈላጊና አጋዥ ነዉ ብለዋል።
የረጲ ሳሙና ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሙፊድ ሳቢና በበኩላቸው በአገር ላይ የመጣውን የጋራ ችግር ለመፍታት በተጋገዝና መደጋገፍ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
የኮሮናቫይረስን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የተለያዩ ተቋማትና ድርጅቶች ድጋፋቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።