ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትናንትና ዛሬ ተካሄደዋል

አዲስ አበባ ሰኔ 24/2010 የ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትናንትና ዛሬ በአዲስ አበባና ክልል ከተሞች ተካሂደዋል። ትናንት በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከምባታ ዱራሜን 37 ለ 34 አሸንፏል። በክልል ከተማ ድሬዳዋ ላይ መከላከያ ድሬዳዋ ከተማን 32 ለ 22 ረቷል። በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም ፌዴራል ፖሊስ ፌዴራል ማረሚያን 28 ለ 26 ሲያሸንፍ፣ መቀሌ ላይ መቀሌ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማን 19 ለ 18 ማሸነፍ ችሏል። የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የሁለት ሳምንት የጨዋታ መርሃ ግብሮች የሚቀሩት ሲሆን የቀጣይ 17ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ሰኔ 30 እና ሐምሌ 1 ቀን 2010  በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ካለፈው ዓመት ጀምሮ እየተካሄደ ያለ ውድድር ሲሆን መከላከያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደውን የሊጉን ውድድር የዋንጫ ባለቤት መሆኑ የሚታወስ ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም