ፈረንሳይ የተመጣጠነ የምግብ እጥረትን ለመቅረፍ 5 መቶ ሺ ዩሮ ለደቡብ ሱዳን ለገሰች

112

መጋቢት 23/2012 ፈረንሳይ የተመጣጠነ የምግብ እጥረትን ለመቅረፍ  5 መቶ ሺ ዩሮ ለደቡብ ሱዳን ለገሰች፡፡

የፈረንሳይ መንግሥት እድሜያቸው ከአምስት አመት በታች የሆኑ 1.3 ሚሊዮን ገደማ ህጻናት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት  ለሚሰቃዩባት  ደቡብ ሱዳን አምስት መቶ ሺ ዮሮ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በሀገሪቱ የተከሰተውን  የተመጠጠነ ምግብ እጥረት ባለፈው ዓመት ያገጠመው የጎርፍ አደጋ  ችግሩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም WFP ከዚህ በፊት በአገሪቱ ለሚገኙ ከ29 ሺ በላይ ነፍሰጡሮችና ህጻናት ምግብ ለማዳረስ አስቸኳይ 170 ሜትሪክ ቶን፣ ገንቢ ምግቦች እንደሚያስፈለግ ገልጾም ነበር፡፡

ይህንንም ተከትሎ ነው የፈረንሳይ መንግስት   ገንቢ ምግብ ለሚያስፈልጋቸው ህጻናትና በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች  ድጋፉን  ለማድግ መወሰኑን በደቡብ ሱዳን የፈረንሳይ አምባሳደር  ማርክ ትሮየት ለራዲዮ ማዛጅ ገልጸዋል፡፡

አምባሳደሩ አክለውም ባለፈው ዓመት የተከሰተው የጎርፍ አደጋ ከዚህ በፊት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ሲሰቃዩ የነበሩትን ህጻናት የበለጠ ሊጎዳ ስለሚችል ፈረንሳይ ድጋፉ የሚያስፈልጋቸውን በመለየት እርዳታውን እንደሰጠች ተናግረዋል፡፡

በ2019 ከተከሰተው ጎርፍ በኋላ በላይኛው የአባይ ተፋሰስ አገራት በተመጣጣነ ምግብ እጥረት የሚሰቃዩ ህጻናት ቁጥር መጨመሩን የምግብ ፕሮግራሙ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም