ቀጥታ፡

በሀዋሳና አዳማ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የኬሚካል ርጭት ተካሄደ

ሀዋሳ/ አዳማ፤ መጋቢት 22/2012 (ኢዜአ) በሀዋሳ እና አዳማ ከተሞች የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል በዋና ዋና መንገዶች ላይ የኬሚካል ርጭት ተካሄደ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ቡሪሶ ቡላሾ እንደገለጹት የጸረ ተህዋሲያን ኬሚካል ርጭቱ የተካሄደው ዛሬ ማለዳ ተጀምሮ እስከረፋዱ አራት ሰዓት ድረስ ነው።

በከተማው 36 ኪሎ ሜትር  በሚሽፍኑ  ዋና ዋና መንገዶች ላይ 360 ኪሎ ግራም የጸረ ተህዋስያን ኬሚካል ጥቅም ላይ መዋሉን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ  በአዳማ ከተማ ዋና ዋና  መንገዶች የኬሚካል ርጭት መካሄዱን የከተማ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት  የሚዲያና ህዝብ አስተያያት ቡድን መሪ አቶ ብሩ ደገፋ ለኢዜአ ገልጸዋል።

"የኬሚካል ርጭቱ የተካሄደው ህዝብ በስፋት የሚንቀሳቀስበት መንገዶች በመለየት ነው "ብለዋል።


በተለይ ከፖስታ ቤት መብራት ኃይል ፣አዳማ ሪፌራል ሆስፒታልና ገዳ ሪዞርት፣ከአዳማ ጌጤ ሆቴል አመዴ፣ከዓለም ሆቴል ሙገር አሰላ መግቢያ ፖስታ ቤት መስመሮች  የኬሚካል ርጭቱ የተካሄባቸው  ናቸው።

በዚህም ከ64ሺህ ሊትር በላይ ኬሚካል ርጭት መካሄዱም ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም