የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ተወያዩ

77

መጋቢት 17/2012 (ኢዜአ)  የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ኮቪድ 19 ቫይረስን መከላከልን በሚቻልባቸው ጉዳዮች  ዙርያ ተወያዩ፡፡

 ውይይት ማድረጋቸውን ታሪፋ የተባለ ድረገጽ የፕሬዝዳንቱን ይፋዊ የትዊተር ድረገጽ ዋቢ በማደረግ ዘገበ።

ኮሮና ቫይረስን እንደአህጉር በጋራ ለመከላከል መደረግ ስለሚኖርባቸው ጥረቶች ከጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ ጋር ስለመወያየታቸው ያነሱት ፕሬዝዳንት ካጋሜ በውይይቱ የካናዳውን ጠቅላይ ሚኒስትር  ጀስቲን ትሩዶንም ተሳትፈዋል፡፡

ካጋሜ  የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ወሳኝ የተባሉ እርምጃዎች መወሰድ እንዳለባቸው  ከመሪዎቹ ጋር መነጋገራቸውን ያነሳው ድረገጹ ኢትዮዽያ ከጃክ ማ ፋውንዴሽን የተገኙትን የእርዳታ ቁሳቁሶች ለአፍሪካ ሃገራት እንዲከፋፈል ያደረገችው ጥረት ያስመሰግናታል ብለዋል።

እሳቸውና የሩዋንዳ ህዝብ ከጃክ ማ ለተደረገላቸው እርዳታ ያመሰገኑት ፕሬዝዳንቱ እገዛው በዚህ አጣብቂኝ ወቅት የተገኘና የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚያስችል አቅም የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል።

ጃክማ እና አሊባባ ፋውንዴሽኖች ለእያንዳንዱ የአፍሪካ ሃገር 20ሺ የመመርመሪያ መሳሪያ 100ሺ የአፍንጫ መሸፈኛ እንዲሁም 1ሺ የመከላከያ አልባሳትን  ማዳረሱን ያነሳው ዘገባው ጠቅላ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ጃክ ማ ባደረጉት ስምምነት መሰረት የኢትዮዽያ አየር መንገድ  እርዳታውን ለሃገራቱ አሰራጭቷል ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም