ቀጥታ፡

ኮቪድ 19ን ለመከላከል የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ የባንክ አካውንቶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ መጋቢት 17/2012 (ኢዜአ)  የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚደረገው ዝግጅት በአምስት ባንኮች የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ አካውንቶች መከፈታቸውን ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሜቴ አስታወቀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኮቪድ19 ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅት የሚውል ገንዘብ እና ሌሎች አቅርቦቶችን የሚያሰባስብ ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ማቋቋማቸው ይታወሳል።

የተቋቋመው የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ማንኛውም መጠን ያለውን የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል የሚከተሉት የባንክ አካውንቶች መከፈታቸውን አስታውቋል።

በዚህ መሰረትም


 1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
 የሂሳብ ቁጥር፦ 1000327017318

 2. አዋሽ ባንክ
 የሂሳብ ቁጥር፦ 0130479475400

 3. ዳሸን ባንክ
 የሂሳብ ቁጥር፦ 0444177190011

 4. ዘመን ባንክ
 የሂሳብ ቁጥር፦ 1032410042463013

 5. አባይ ባንክ
 የሂሳብ ቁጥር፦ 1022115562778011

ኮሚቴው ተጨማሪ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቆ "እስከዚያ ድረስ ግን 'ተረጋግተን አስተዋጽኦ እናድርግ'፤ ችግሩን በአብሮነት እንወጣዋለን" ሲል መልዕክት አስተላልፏል።

መንግሥት በጀት መደቦ የመጨረሻው አስከፊ ሁኔታ ቢከሰት ለመቋቋም የሚያስችሉ ግብአቶችን በማሰባሰብ ላይ ይገኛል።

ይህን ተከትሎ በቀዳሚነት ተግባራዊ በማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የብሔራዊ ኮሚቴው አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለብሔራዊው የኮቪድ19 ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ መለገሳቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም