ቀጥታ፡

የኮሮናን ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል ሕዝበ ሙስሊሙ በቤቱ መስገድ ይችላል ተባለ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2012(ኢዜአ) የኮሮናቫይረስ ስርጭት ስጋትን ለመቀነስ ሕዝበ ሙስሊሙ በቤቱ መስገድ እንደሚችል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አስታወቀ።

የምክር ቤቱ የዑለማ ምክር ቤት የኮሮናን ቫይረስ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫውም የኮሮና ቫይረስ አስጊ በሆነበት በዚህ ሁኔታ ከጁምዓ እና ጀመዓ መቅረት በሸሪዓ የተፈቀደ በመሆኑ ሙስሊሙ በየቤቱ መስገድ እንደሚችል አስታውቋል።

በቫይረሱ የተያዘ ወይም የተጠረጠረ ሰው ለጁምዓም ሆነ ለጀመዓ ሶላት እና ለሃይማኖታዊ ትምህርት ወደ መስጊድና ህዝብ ወደተሰበሰበበት አካባቢ መምጣት የተከለከለ እንደሆነም ገልጿል።

የጤና ተቋማትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትም ምክርና መመሪያ መቀበልና በስራ ላይ ማዋል ሃይማኖታዊ ግዴታ መሆኑንም የምክር ቤቱ መግለጫ አመልክቷል።

የመስጂድ ኢማሞች፣ ዑለሞች እና ዳዒዎች ሙስሊሙን ወደ አላህ እንዲመለስና ምህረት እንዲለምን፣ ሰደቃ እንዲሰጥና ዱዓ እንዲያደርግ እንዲመክሩ እንጠይቃለንም ብሏል ምክር ቤቱ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም