የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮረና ቫይረስን ለመከላከል የሚያግዝ ቁሳቁስ ሊያጓጉዝ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮረና ቫይረስን ለመከላከል የሚያግዝ ቁሳቁስ ሊያጓጉዝ ነው
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2012 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዳ ቁሳቁስ ከቻይና ሊያመላልስ መሆኑን ተገልጿል።
ለአፍሎጀስቲክስ አብዴት የተባለው እንደዘገበው የመከላከያ ቁሳቁሱ ከቻይና ወደ ኢትዮጵያና ቫይረሱ ወደ ተስፋፋባቸው ሀገሮች የሚከፋፈለው ዶክተር አብይ አሕመድ ከአሊባባ ቡድን መሥራችና ሥራ አስፈጻሚ ጃክማና ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በተደረሰ ስመምነት መሠረት ነው።
መጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በቦይንግ 777 አውሮፕላንን 108 ቶን በላይ የመመርመሪያ መሳሪያዎችን፣ የፊትና የአፍ መሸፈኛ ጭንብሎችን እና ሌሎች መከላከያዎችንም ኢትዮጵያን ማዕከል አድርጎ ለተቀሩት የአፍሪካ ሀገራት እንዲዳረስ እንደሚደረግ ዘገባው አመልክቷል።
የአሊባባና የጃክ ማ ፋውንዴሽን መሥራች ጃክ ማ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የፊት መሸፈኛ ጭብሎችን፣ የቤተ ሙከራ ቁሳቁሶችንና ሌሎች የህክምና መስጫ ግብዓቶችን ለአሜሪካ፣ ለአፍሪካ፣ ለስፔን፣ለስሎቬኒያ እና ፈረንሳይ ለመላክ ቃል መግባታቸውን በዘገባው ተጠቅሷል።
በዚህ ጊዜ ቫይረሱን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ወቅታዊ መረጃና ቁሳቁስ ማቅረብ እንደሚገባ ያስታወሰው ዘገባው፤ ቫይረሱን ለመከላከል በቂ መሠረተ ልማት ላላሟሉ የአፍሪካ ሀገራት ኮቪድ 19 አደገኛ ሁኔታ ሊፈጥር እንደሚቸል አመልክቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ዓለም አቀፍ የንግድ መሰናክሎችን ለመቀነስና የገቢና የወጪ ንግዶች ዝውውርን ለማቀላጠፍ የኤሌክትሮኒክስ የንግድ ሥርዓትን በኢትዮጵያ ለማስተዋወቅ ከአሊባባ ግሩፕ ጋር እየሠሩ እንደሚገኙም ዘገባው አመልክቷል።