ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 ሀገራት የሚያደርገውን በረራ አቋረጠ

አዲስ አበባ ፣መጋቢት 11/2012 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 ሀገራት የሚያደርገውን በረራ አቋረጠ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 ሃገራት የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን  ገልጸዋል።

ከየትኛውም ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ለ14 ቀናት በልዩ ማቆያ የመቆየት ግዴታ  እንደተጣለባቸውና  ወጭውም በግለሰቡ እንዲሸፈን ተወስኗል ብለዋል።

በማረሚያ ቤቶች ቫይረሱ ከገባ ለቁጥጥር አስቸጋሪ በመሆኑ በተለይ ህጻናትን የያዙ፣ የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሰና  ሊፈቱ ጥቂት ቀን የቀራቸው ታራሚዎች እንዲፈቱ መወሰኑንም አስታውቀዋል።

የህግ ታራሚዎችንም ማንኛውም ሰው እንዲጠይቅ የማይፈቀድለት መሆኑን ጠቁመዋል።

በየከተማው የሚገኙ የመጠጥና የምሽት ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ ሥራቸውን እንዲያቋርጡ የተወሰነ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ቤተ እምነቶች በሚሰባሰቡበት ወቅት ለቫይረሱ ሊጋለጡ ስለሚችሉ ችግሩን ለመፍታት ተነጋግረው መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም