በወላይታ እና ቦንጋ ዲስትሪክት ስር የሚገኙ ከተሞች የኤሌክትሪክ መብራት እንደሚቋረጥባቸው ተገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
በወላይታ እና ቦንጋ ዲስትሪክት ስር የሚገኙ ከተሞች የኤሌክትሪክ መብራት እንደሚቋረጥባቸው ተገለጸ
ሀዋሳ መጋቢት 11/2012 ( ኢዜአ) በደቡብ ክልል ወላይታና ቦንጋ ዲስትሪክት ስር የሚገኙ ከተሞች ለ15 ቀናት የኤሌክትሪክ መብራት አገልግሎት የሚቋረጥባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
በአገልግሎቱ የደቡብ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ታሪኩ ዛሬ እንደገጹት አገልግሎቱ የሚቋረጠው በኮንታ ልዩ ወረዳ "አባ " የተባለው የማከፋፈያ ጣቢያ በመሬት ናዳ ጉዳት ስለደረሰበት ነው።
በዚህ ምክንያት በሁለቱ ዲስትሪክቶች ስር የሚገኙ ተርጫ፣ቶጫ፣ገሳና ኮንታ ማዕከላት ስር የሚገለገሉ ደንበኞች ከመጋቢት 15 እስከ 30 ቀን 2012ዓ.ም ድረስ የኤሌክትሪክ መብራት እንደሚቋረጥባቸው አስታውቀዋል።
መብራት በሚጠፋባቸው ቀናት የማስተካከል ስራዎች ስለሚካሄዱ ህብረተሰቡ ይህንን ተረድቶ በትዕግስት እንዲጠበቅና ከወዲሁ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግም ስራ አስኪያጁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።