በደቡብ አፍሪካ ኮሮና ቫይረስን ይፈውሳል በሚል ፈሳሽ ሳሙና የጠጡ 59 ሰዎች ሞቱ

92

መጋቢት 10/2012 (ኢዜ አ) በደቡብ አፍሪካ ኮሮና ቫይረስን ይፈውሳል በሚል ፈሳሽ   ሳሙና  የጠጡ 59 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ፡፡

በደቡብ አፍሪካ አንድ የሃይማኖት መምህር   ከኮሮና  ቫይረስ  ትፈወሳላችሁ በሚል ፈሻስ ሳሙና ለተከታዮቹ  በማጠጣቱ የ59 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሌሎች አራት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ኬኒያቱደይ አስነብቧል፡፡

የሀገሪቱ ፖሊስ ጉዳቱን ያደረሰውን መምህር ክትትል እያደረገበት  እንደሆነ ሲገልጽ  ህብረተሰቡ ከመሰል ድርጊቶች እንዲቆጠብም   አሳስቧል፡፡

 ፖሊስ አክሎም ወረርሽኙ አለም አቀፍ በመሆኑ ቫይረሱን ለመከላከል የህክምና ባለሞያዎች ምክር ብቻ ተግባራዊ እንዲያደርጉም መክሯል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም