ቀጥታ፡

አሜሪካና እስራኤል በውሀ ማጣራትና መልሶ ጥቅም ላይ የሚሰራ መርሃ ግብር ይፋ አደረጉ

መጋቢት 7/2012 ( ኢዜአ) አሜሪካና እስራኤል በ21 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር የሚከናወን የውሃ ኃይል ፕሮግራም ይፋ አደረጉ።

ፕሮግራሙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በውሀ ስርጭት፣ ማጣራትና በመልሶ ጥቅም ላይ ትኩረቱን ያደርጋል ተብሏል፡፡

በቤን ጎሪዎን ዩኒቨርሲቲ 'ኦፍ ኔጊቭ ' የቴክኖሎጂ ተቋም ከኖርዝ ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የሃይል እጥረት የሚፈታ ፕሮግራም ነው ይፋ የተደረገው፡፡

በሁለት የአሜሪካና እስራኤል  ተቋማት ጥምረት የሚመራው ፕሮግራሙ በንጹህ ውሃ ስርጭት፣ ሃይል ማመንጨት  አቅርቦት እና ማጣራት ላይ በዋናነት የሚሰራ ይሆናል፡፡

በአሁኑ ወቅት በከተሞች የሚካሄደው ንጹህ ውሃን የማጣራት ሂደት ከተሞቹ ከሚያስፈልጋቸው መጠን በላይ የሚከናወን በመሆኑ ፤ ፕሮግራሙ ያለ አግባብ የሚባክነውን ውሀ መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋልና በንጥረ ነገሮች የታገዘ ውሃ ለህብረተሰቡ ለማዳረስም የሚያገለግል ነው ተብሏል፡፡

የፕሮግራሙ የሙከራ ስራዎች በአሜሪካና እስራኤል በሚገኙ የውሃ ስርጭትና ማጣራት ተቋማት ውስጥ ከተከናወነ በኋላ በመላው አለም እንደሚተገበርም ተነግሯል፡፡

21 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተመደበለት ፕሮግራሙ በእስራኤልና አሜሪካ የሚገኙ የኢኖቪሽንና የኢነርጂ ተቋማት ክትትልና ድጋፍ እንደሚደርግለትም 'ጄሩሳሌም ፖስት' አስነብቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም