በትግራይ ክልል አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ተጀመረ

71

መቀሌ፤ መጋቢት 5/2012 (ኢዜአ) በትግራይ ክልል አቀፍ የአትሌቲክስ ውድርር ዛሬ በመቐለ ተጀምሯል። 

የትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ማሞ እንደገለፁት ውድድሩ የፊታችን ሚያዝያ ወር በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የአትሌቲክስ ሻምፕዮና ክልሉን ወክለው የሚሳተፉ  ብቃት ያላቸው አትሌቶችን ለመምረጥ የተዘጋጀ ነው ።

ዛሬ የተጀመረው ውድድር በተለያዩ የአትሌቲክስ ዘርፎች ለአንድ ሳምንት እንደሚካሔድም አቶ ጌታቸው ተናግረዋል ።

በክልሉ የአትሌቲክስ ውድድር ዳኞች ፕሬዚዳንት  አቶ ቢንያም ሂወት በበኩላቸው ውድድሩ ከአጭር፣ መካከለኛና ረጅም ርቀት ሩጫ በተጨማሪ በሁለቱም ፆታዎች የአሎሎና የዲስከስ ውርወራ፣ የከፍታና የርዝመት ዝላይ ጨዋታዎችን ያካተተ ነው ።

በውድድሩ ከ25 ወረዳዎችና ከ6 ክለቦች የተውጣጡ  400   አትሌቶች ይሳተፋሉ ብለዋል ።

በ10 ሺህ ሜትር ሩጫ የሚወዳደረው አትሌት ምህረት ተፈሪ በሰጠው አስተያየት በውድድሩ በማሸነፍ በቀጣይ በዓለም አቀፍ ውድድሮች የአገሩንና የክልሉን ስም ለማስጠራት ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም