ምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልሎች ፍኖተ ካርታን ይፋ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልሎች ፍኖተ ካርታን ይፋ አደረገ
መጋቢት 05/2012 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልሎች ፍኖተ ካርታን ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ይህ የምርጫ ክልሎች ፍኖተ ካርታ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀ መሆኑን የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ገልፀዋል።
ፍኖተ ካርታው የተለያዩ ጥናቶች ተደርገው እንደተሰራ ወ/ሪት ብርቱካን አክለው ገልጸዋል።
በፍኖተ ካርታው ላይ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች የተካፈሉበት ውይይትም ተካሂዷል።
ፍኖተ ካርታው በ2007 የተካሄደውን የህዝብ ቆጠራ እንደ መነሻ በመውሰድ መሰራቱን የቦርድ ሰብሳቢዋ ተናግረዋል።
በዚሁ መሰረት ትግራይ ክልል 38፣ አፋር 8፣ አማራ 138፣ ኦሮሚያ 178፣ ሶማሌ 23፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 9፣ ደቡብ (የተለየ ውክልና የሚሰጣቸው 15 የምርጫ ክልሎች ተካተውበት) 123፣ ጋምቤላ 3፣ ሀረሪ 2፣ ድሬዳዋ 2 እና አዲስ አበባ 23 የምርጫ ክልሎች (ለፌደራል የህዝብ ምክር ቤት) ይኖራቸዋል።
በአጠቃላይ 547 የምርጫ ክልሎች ይፋ ተደርገዋል።
(ኢቢሲ)