የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ሰራተኞች በቦንብ ጥቃት ለተጎዱ ዜጎች ደም ለገሱ - ኢዜአ አማርኛ
የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ሰራተኞች በቦንብ ጥቃት ለተጎዱ ዜጎች ደም ለገሱ
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2010 የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ሰራተኞች በመስቀል አደባባይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት ለተጎዱ ወገኖች ደም ለገሱ። ሰራተኞቹ በብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ደም በለገሱበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ለመደገፍ በመስቀል አደባባይ በነበረው ሰልፍ በደረሰው አደጋ ማዘናቸውን ተናግረዋል። በፅህፈት ቤቱ የባለ-ብዙ ዘርፍ ዳይሬክተር ወይዘሮ አለሚቱ ጉዲሳ ሰራተኞቹ ለተጎዱ ወገኖችው ደም በመለገስ ህይወታቸውን ለመታደግ እንደመጡ ተናግረው ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ደም በመለገስ የተጎዱትን መደገፍ እንዳለበትም ነው የገለፁት።
"በወገኖቻችን ላይ ለደረሰው ጥቃት ደም ለመስጠት ነው የመጣሁት ፤እኔ መስጠት ከቻልኩኝ የአንድ ሰው ህይወት እንኳን ባድን ብዬ ነው " በማለት የተናገረችው የፅህፈት ቤቱ ሰራተኛ ወይዘሮ አበባ ተሾመ ናቸው፡፡ ሁሉም ዜጋ ለውጡን በመደገፍ አንድ ኢትዮጵያን ለመፍጠር መረባረብ እንዳለበትም ነው የተናገሩት። በተመሳሳይ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ሚኒስቴር ሰራተኞች በሰልፉ ዜጎች ላይ የደረሰውን አደጋ ተከትሎ ደም ለግሰዋል። ሚኒስትሩ አቶ ታገሰ ጫፎ እንዳሉት ሰራተኞቹ ልገሳውን ያደረጉት ለወገኖቻቸውን ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት ነው። በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን አስወግዶ በቅንነት ማገልገል ሰራተኛው የአገሪቱ የለውጥ ጉዞ አጋዥ መሆን እንደሚገባውም ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ወደ ኃላፊነት ከመጡ በኋላ ለተመዘገቡ ለውጦች ድጋፍና ዕውቅና ለመስጠት ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በተጠራ ሰልፍ ላይ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት ሁለት ሰዎች ሲሞቱ ከ150 በላይ በሚሆኑ ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።