ቀጥታ፡

በግማሽ ቢሊዮን ብር የተገነባው የትምህርት ተቋም አገልግሎት ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ መጋቢት 4/2012(ኢዜአ) ግማሽ ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ካብሪጅ አካዳሚ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ መጀመሩን ይፋ አደረገ።

አካዳሚው የእንግሊዝን ስርዓተ ትምህርት ከኢትዮጵያ ጋር በማቀናጀት አለም ዓቀፍ ደረጃ ያለው ትምህርት የሚሰጥበት እንደሆነ ተገልጿል።

የትምህርት ቤቱ ግንባታ 500 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ሰሚት አካባቢ  በ30 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ አርፏል።

ትምህርት ቤቱ ምቹ የመማር ማስተማር ስርዓት ለመዘርጋት የሚረዱትን  ደረጃቸውን  የጠበቁ 200 የመማሪያ ክፍሎች ፣ የተሟላ የስፖርት ማዘውተሪያ፣የተሟላ  ላብራቶሪ  የተዘጋጀለት መሆኑ ተገልጿል።

የትምህርት አሰጣጥ ስርዓቱ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሌሎች ተጨማሪ ቋንቋዎች በማካተት የሚሰጥበት እንደሆነ  በአካዳሚው መስራች ዶክተር ገመችስ ደስታ ተጠቅሷል።

ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚያስተምረው አካዳሚ በአገሪቱ ጥራት ያለው ትምህርት ለማዳረስ የተቀመጠውን ግብ የሚደግፍ ነው ተብሏል።

አካዳሚው ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት የራሱን መስፈርት በማውጣት  ለተማሪዎች  የነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥም ታውቋል።    

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም