ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በኬንያ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በኬንያ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ
መጋቢት 4/2012 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በናይሮቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውንን አግኝተው አነጋገሩ፡፡
የስራ ጉብኝት ለማድረግ መጋቢት 3 /2012 ዓ.ም ናይሮቢ የገቡት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኬንያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ አባላት ጋር በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በኤምባሲው ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ኢትዮጵያ እየገነባችው ስላለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር እየተደረገ ስላለው ድርድር በሰፊው አብራርተዋል፡፡
ፕሬዝዳንቷ በንግግራቸው ታላቁ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ እየተሳተፉበት ያለ የህዝብ ፕሮጀክት መሆኑን በመግለፅ በውጭ የሚኖሩ ዜጎች እስካሁን ላደረጉት ድጋፍ አመስግነው የበለጠ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሌላ በኩል የዳያስፖራ አባላቱ የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን በማንሳት ፕሬዝዳንቷ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በናይሮቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ አባላት በግድቡ የድርድር ሂደት ላይ መንግስት የያዘውን አቋም አድንቀው፤ የበለጠ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል መግባታቸው ተነግሯል፡፡
ምንጭ፡-የኢትዮጵያ ኢምባሲ በኬንያ