በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሙያዊ ምክክር በመካሄድ ላይ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሙያዊ ምክክር በመካሄድ ላይ ነው
አዲስ አበባ መጋቢት 4/2012 (ኢዜአ) በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በእውቀት ላይ ተመስርቶ የህዝብ ተሳትፎና አገራዊ ጥቅምን በሚያስጠበቅ መልኩ ለመደራደር የሚያስችል ምክክር እየተደረገ ነው።
በምክክሩ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች፣ የሃይማኖት አባቶቾችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ተሳትፈውበታል።
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀው የምክክር መድረክ ህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ በመያዝ በግንባታው ሂደት ላይ ድጋፍ እንዲያደርግና አገራዊ ጥቅምን የሚያስጠብቅ ድርድር ለማካሄድ ያስችላል ተብሏል።