ቀጥታ፡

ምክር ቤቱ የሚኒስትሮችን ሹመት አፀደቀ

አዲስ አበባ መጋቢት 3/2012 (ኢዜአ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ሚኒስትሮችን ሹመት አፀድቋል።

ምክር ቤቱ በዛሬው  እለት አምስተኛ  ዓመት  የስራ ዘመን  14ኛ  መደበኛ  ስብሰባውን  አካሂዷል።

በመደበኛ ስብሰባውም በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የቀረበለትን የተለያዩ የሚኒስትሮች ሹመት ተቀብሎ አጽድቋል።

በዚህ መሰረት:-

1 ወይዘሮ አዳነች አቤቤ - የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

2 ዶክተር ሊያ ታደሰ - የጤና ሚኒስትር

3 አቶ ላቀ አያሌው - የገቢዎች ሚኒስትር

4 ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ - የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የፌዴራል ስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና  ኮሚሽን  ኮሚሽነርን  ሹመት  አፅድቋል።

በዚህ መሰረት አቶ ፀጋ አራጌ - የፌዴራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን  ኮሚሽነር  በመሆን ተሹመዋል።

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አመራር አባላት ሹመትንም ያፀደቀ ሲሆን

ክቡር አቶ አወሉ አብዲ------ የቦርዱ ሰብሳቢ

አቶ ጌትነት ታደሰ ------ ፀሃፊ

ወይዘሮ አበበች ሺክታ ------- አባል

ዶክተር አጋረደች ጀማነህ ---አባል

ዶክተር ወዳጄነህ መሃረነ ---አባል

አቶ ኡባንግ ሜቶ----------አባል

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት -----አባል

አቶ ማንያዘዋል እንደሻው ----አባል

ዶክተር ኮንቴ ሙሳ -----አባል ሆነው የተሾሙ ሲሆን ምክር ቤቱ ሹመቶችን በአብላጫ ድምጽ አጽድቋቸዋል።  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም