ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ ባለፈው ዓመት ለሞቱ የተመድ ሰራተኞች መታሰቢያ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1/2012  ዓ.ም (ኢዜአ) በቦይንግ 737 ማክስ 8 የአውሮፕላን አደጋ ባለፈው ህይወታቸውን ላጡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ሰራተኞች የመታሰቢያ ፕሮግራም ተከናወነ።


በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በተከናወነው ፕሮግራም በተመድ ስር የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅት ኃላፊዎችና የሟች ቤተሰቦች በታደሙበት የመታሰቢያ መርሃ ግብሩ ተካሂዷል።

በስነስርአቱ ላይም በእለቱ ታዳሚዎች ለሟቾቹ የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737 – 800 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ መላውን ዓለም አሳዝኖ አልፏል።

አውሮፕላኑ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ በመጓዝ ላይ ሳለ ከስድስት ደቂቃ በኋላ ከበረራ ተቆጣጣሪዎች ጋር ግንኙነቱ ተቋርጦ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ቢሾፍቱ አካባቢ መከስከሱ ይታወሳል።

በአደጋው ከ30 በላይ አገራት ዜጎች በጥቅሉ የ157 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ከሟቾቹ መካከል 21ዱ የተመድ ሰራተኞች ነበሩ።

አፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሀፊ ቬራ ሶንግዌ በመታሰቢያ መርሃ ግብሩ ላይ በአሳዛኙ ክስተት ያለፉ የድርጅቱን አባላት ሁልጊዜም እናስባቸዋለን ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም