ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ገብተዋል

አዲስ አበባ የካቲት 28/2012 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ለመወያየት ዛሬ ማለዳ ላይ በደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ገብተዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ከተማዋ ሲገቡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው እና የዞኑ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በዞኑ በሚኖራቸው ቆይታ በታርጫ ስታዲየም ለአካባቢው ነዋሪዎች ንግግር ያደርጋሉ።

ከሠዓት በኋላም ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ የአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሠላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በከተማዋ ተገኝተዋል።  

በአሁኑ ሰአት በተርጫ ስታዲየም ከዳውሮ ዞን አስር ወረዳዎች የተውጣጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች  የተገኙ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ  በአሁኑ ወቅትም ተርጫ ስታዲየም ደርሰዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም