ቀጥታ፡

በሀገረ አቀፈ ደረጃ ሁሉንም ባለድርሻ አካል የሚያስተሳስር የሎጀስቲክ ሥርዓት ገና አለመዘርጋቱን የሎጂስቲክስ ማኅበረሰብ ፕሬዚዳንት አስታወቀ

የካቲት 27/2012 (ኢዜአ) መንግሥት የግሉን ዘርፍ ዕድገት ለማበረታታት እና ማነቆዎችን ለማስወገድ ብሔራዊ የሎጂስቲክ  ስትራቴጂ ነድፎ እየሠራ መሆኑን የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ገልጸዋል።

የሎጂስቲክስ ማኅበረሰብ  ፕሬዘዳንቷ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ጌታሁን ዛሬ የካቲት 27 ቀን 2012 "የሎጅስቲክስ ዘርፍ የሪፎርም" በሚል ርዕስ በተካሄደው የአዲስ ወግ መረሐግብር ላይ እንደተናገሩት ፤ በሀገር ደረጃ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚያስተሳስር የሎጂስቲክስ ስርዓት ገና ባለመፈጠሩ የሎጂስቲክስ ምክር ቤት ማቋቋም ያስፈልጋል።

የምክር ቤቱ መቋቋም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚያስተሳስር የሎጀስቲክ ሥርዓት ለመፍጠርም አይነተኛ ሚና እንዳለውም አሳስበዋል።

የሎጂስቲክስ ዘርፍን ስናስብ የጊዜና የገንዘብን ዋጋ ከግምት ውስጥ ማስገባት አለብን ያሉት ፕሬዘዳንቷ ፤ በመንግሥት እየተወሰዱ ያሉት ማሻሻያዎች ጥሩ ቢሆኑም ፣ቀጣይ እርምጃዎች መውሰድ ላይ መፋጠን እንደሚገባ ገልጸዋል።

የሎጂስቲክ ልማት ቁልፍ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ መሆኑ ሊስተዋል እንደሚገባም አስረድተዋል።

የሎጂስቲክ ዘርፍ ከፍተኛ መሻሻል እንዲታይበት ሥራዎች በአፋጣኝ ሊከናወኑ ያስፈልገዋል ያሉት ደግሞ ዶ/ር ማቴዎስ ኢንሰርሙ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ናቸው።

የኢትዮጵያ ሎጂስቲክ  ስትራተጂያዊ አቀማመጥ ለምሥራቅ አፍሪካ እጅግ ጠቃሚ ቢሆንም ፣በእሴት ላይ እምብዛም ዋጋ ባለመጨመራችን እና ሥራው ያለቀለት ምርት የምናስገባ መሆኑ አሉታዊ ጎንናችን ነው ሲሉ ዶክተር ማቴዎስ ተናግረዋል ።

የማሪታይም ጉዳዮች ባለስልጣን ዳይሬክተር ጀነራል አቶ መኮንን አበራ በበኩላቸው ፤ የሎጂስቲክ ሥርዓቱ ማነቆዎችን ከነመንስኤያቸው መለየት፣ የመፍትሔ ሀሳቦችን ወደ መርሀግብር ለውጦ መተግበርና እንዲያውም ወደ አንድ የኢንደስትሪ ዘርፍ እንዲያድግ የሚያስችሉ ሥራዎች ተሠርተዋል።

የግሉዘርፍአስተዋጽኦየዳበረእንዲሆንመንግሥትእሴትንለመጨመርሊያደርግየሚያስፈልገውድጋፍተለይቶታውቋልያሉትአቶሮባመገርሳየኢትዮጵያየባህርትራንስፖርትእናሎጂስቲክአገልግሎትድርጅትቺፍኤክስኪውቲቭኦፊሰርናቸው።

ለዚህምዓይነተኛማሳያየሚሆነውበደረቅወደቦችላይእየተሠራያለውሥራነውሲሉምአቶሮባተናግረዋል።

"የሎጅስቲክስ ዘርፍ የሪፎርም" በሚል ርዕስ በአዲስ ወግ መረ ሐግብር እየተከሄደ ያለው ውይይት እየተካሄደ እንደሚገኝ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያ ። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም