ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ የአርኪዎሎጂ እና ጥንታዊ ታሪክ መዳረሻ ሀገር በሚል ተሸለመች

የካቲት 27/2012 (ኢዜአ) በጀርመን በየአመቱ በሚካሄደው የአርኪዎሎጂ እና ጥንታዊ ታሪክ መዳረሻ ሀገር PATWA-Award (Pacific Area Travel Writers Association-Award) አሸናፊ መሆኗን የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዚም ሚኒቴር አስታወቀ።

ሚኒቴሩ በተጨማሪ የኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው በዚሁ

የ PATWA ሽልማት ላይ ከሰሃራ በታች ምርጥ የቱሪዝም ሚኒስትር ሽልማትን ማግኘታቸውንም አስታውቋል።

የፓትዋ ሽልማት በየአመቱ በጀርመን በሚካሄደው እና በአለማችን ዕውቅ በሆነው ITB (Internationale Tourismuse Börse-Berlin) የቱሪዝም ንግድ ትርዒት ላይ የሚሰጥ የእውቅና ስነ-ስርዓት ነው።

በዘንድሮው የፓትዋ ሽልማት በተለያዩ ዘርፎች አስራ ሶስት የዓለም ሀገራት ያሸነፉ መሆናቸውን ያስታወቀው ሚኒስቴሩ፤ ኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ የአርኪዎሎጂ እና ጥንታዊ ታሪክ መዳረሻ ሀገር በሚለው ዘርፍ በቀዳሚነት አሸናፊ መሆኗን አረጋግጧል።

 
በተጨማሪም ዶ/ር ሂሩት ካሳውን ጨምሮው አምስት የተለያዩ ሀገራት ሚንስትሮች የምርጥ ቱሪዝም ሚኒስትርነትን ሽልማት ማግኘታቸውምንም ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም